በድምጽ መስጫ ቀን የተከለከሉ ተግባራት ምን ምን ናቸው ?
በድምጽ መስጫ ቀን የተከለከሉ ተግባራት ምን ምን ናቸው ?
• ማንኛውም ሰው ከምርጫ ጣቢያው 200 ሜትር ዙሪያ መለስ ርቀት ውስጥ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ፣ የጦር መሣሪያ ይዞ ወይም በሌላ በማናቸውም ፀጥታን በሚያደፈርስ ሁኔታ ውስጥ መገኘት የለበትም
• መራጭ ያልሆኑና ድምፅ የሰጡ ሰዎች በምርጫ ጣቢያው ውስጥ መገኘት የለባቸውም
• ማንኛውም ሰው ያለፈቃድ ወደምርጫ ጣቢያው በመግባት / በምርጫ ጣቢያው ግቢ ውስጥም ሆነ ውጭ የምርጫውን እንቅስቃሴ ማወክ ወይም ማደናቀፍ ወይም ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴ ማድረግ የለበትም
ወደ ምርጫ ጣቢያ የማይገቡ ነገሮች ምንድናቸው?
• ማንኛውም ሰው እንደ በራሪ ወረቀት፣ ፖስተር እና በሌሎች አጭር ጽሁፍ መልክ የተዘጋጁ የምርጫ ቅስቀሳ ሰነዶችን ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያው መግባት አይችልም፡፡
• ማንኛውም ሰው የጦር መሳሪያ ወይም እንደጩቤ እንደ ሴንጢ የመሳሰሉ ስለትነት ያላቸውን ወይም እንደየአካባቢው ሁኔታ ለሀይል መጠቀሚያነት የሚውሉ እንደዱላ ፣ አለንጋ ፣ ቁራጭ እንጨት ወይም ብረት ወይም ሌላ ማንኛውንም ተቀጣጣይ ወይም የሚፈነዳ ጠጣር ወይም ፈሳሽ ነገር ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያ መግባት የለበትም።
• ከላይ የተዘረዘሩትን የተከለከሉ ነገሮች ወደምርጫ ጣቢያ ይዞ የመጣ መራጭ የምርጫ ጣቢያው የሰልፍ አስከባሪ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት በአደራ አስቀምጦ መግባት አለበት።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ
Comments
Post a Comment